2 ሳሙኤል 22:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ይሖዋን ጠራሁት፤+አምላኬን ደጋግሜ ጠራሁት። እሱም በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፣እርዳታ ለማግኘት የማሰማውም ጩኸት ወደ ጆሮው ደረሰ።+ 2 ዜና መዋዕል 20:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ‘ሰይፍ፣ የቅጣት ፍርድ፣ ቸነፈር ወይም ረሃብ በእኛ ላይ ጥፋት ቢያደርስብን በዚህ ቤትና በአንተ ፊት እንቆማለን (ይህን ቤት ለስምህ መርጠኸዋልና)፤+ ከጭንቀታችንም እንድትገላግለን ወደ አንተ እንጮኻለን፤ አንተም ሰምተህ አድነን።’+ 2 ዜና መዋዕል 32:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ንጉሥ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ+ ግን ይህን ጉዳይ በተመለከተ አጥብቀው ጸለዩ፤ እርዳታ ለማግኘትም ወደ ሰማይ ጮኹ።+ መዝሙር 50:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በጭንቅ ቀን ጥራኝ።+ እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታወድሰኛለህ።”+
9 ‘ሰይፍ፣ የቅጣት ፍርድ፣ ቸነፈር ወይም ረሃብ በእኛ ላይ ጥፋት ቢያደርስብን በዚህ ቤትና በአንተ ፊት እንቆማለን (ይህን ቤት ለስምህ መርጠኸዋልና)፤+ ከጭንቀታችንም እንድትገላግለን ወደ አንተ እንጮኻለን፤ አንተም ሰምተህ አድነን።’+