-
ኢሳይያስ 37:23-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ያቃለልከውና+ የሰደብከው ማንን ነው?
ድምፅህን ከፍ ያደረግከው፣+
እብሪተኛ ዓይንህንም ያነሳኸው በማን ላይ ነው?
በእስራኤል ቅዱስ ላይ እኮ ነው!+
24 በአገልጋዮችህ በኩል ይሖዋን አቃለሃል፤+ እንዲህም ብለሃል፦
‘ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎቼ፣
ወደ ተራሮች ከፍታ፣
ርቀው ወደሚገኙትም የሊባኖስ ስፍራዎች እወጣለሁ።+
ረጃጅሞቹን አርዘ ሊባኖሶች፣ ምርጥ የሆኑትንም የጥድ ዛፎች እቆርጣለሁ።
እጅግ ከፍ ወዳለው ማረፊያ ቦታ፣ በጣም ጥቅጥቅ ወዳለው ጫካ እገባለሁ።
25 ጉድጓድ ቆፍሬ ውኃ እጠጣለሁ፤
የግብፅን ጅረቶች* በእግሬ ረግጬ አደርቃለሁ።’
-