የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 24:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+ 13 ከዚያም በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ወሰደ።+ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሰለሞን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ የሠራቸውን የወርቅ ዕቃዎች በሙሉ ሰባበራቸው።+ ይህ የሆነው ይሖዋ አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው።

  • 2 ነገሥት 25:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ከለዳውያኑም የይሖዋን ቤት የመዳብ ዓምዶች+ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ የነበሩትን የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችና+ የመዳብ ባሕር+ ሰባብረው መዳቡን ወደ ባቢሎን አጋዙ።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ናቡከደነጾርም በይሖዋ ቤት ያሉ የተወሰኑ ዕቃዎችን ወደ ባቢሎን ወስዶ በባቢሎን በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ አስቀመጣቸው።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 በእውነተኛው አምላክ ቤት የነበሩትን ትላልቅም ሆኑ ትናንሽ ዕቃዎች በሙሉ፣ የይሖዋን ቤት ውድ ሀብት እንዲሁም የንጉሡንና የመኳንንቱን ውድ ሀብት ሁሉ ወደ ባቢሎን አጋዘ።+

  • ኤርምያስ 27:21, 22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 አዎ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ በይሖዋ ቤት፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤትና* በኢየሩሳሌም ስለቀሩት ዕቃዎች እንዲህ ይላል፦ 22 ‘“ትኩረቴን ወደ እነሱ እስከማዞርበት ጊዜ ድረስ ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤+ በዚያም ይቆያሉ” ይላል ይሖዋ። “ከዚያ በኋላ አመጣቸዋለሁ፤ ወደዚህ ስፍራም እመልሳቸዋለሁ።”’”+

  • ዳንኤል 1:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንና በእውነተኛው አምላክ ቤት* ውስጥ ካሉት ዕቃዎች መካከል የተወሰኑትን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤+ እሱም በሰናኦር+ ምድር* ወደሚገኘው ወደ አምላኩ ቤት* አመጣቸው። ዕቃዎቹን በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አስቀመጣቸው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ