-
ኤርምያስ 27:19-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ዓምዶቹ፣+ ስለ ባሕሩ፣*+ ስለ ዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹና+ በዚህች ከተማ ስለቀሩት የተረፉ ዕቃዎች እንዲህ ይላልና፦ 20 እነዚህ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር የኢዮዓቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባጋዘበት ወቅት ሳይወስዳቸው የቀሩ ነገሮች ናቸው፤+ 21 አዎ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ በይሖዋ ቤት፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤትና* በኢየሩሳሌም ስለቀሩት ዕቃዎች እንዲህ ይላል፦ 22 ‘“ትኩረቴን ወደ እነሱ እስከማዞርበት ጊዜ ድረስ ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤+ በዚያም ይቆያሉ” ይላል ይሖዋ። “ከዚያ በኋላ አመጣቸዋለሁ፤ ወደዚህ ስፍራም እመልሳቸዋለሁ።”’”+
-