ዘሌዋውያን 22:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ቅዱሱን ስሜን አታርክሱ፤+ እኔ በእስራኤላውያን መካከል ልቀደስ ይገባኛል።+ የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ፤+ ኢሳይያስ 45:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 የእስራኤል ዘር ሁሉ በይሖዋ ትክክለኛ ሆኖ ይገኛል፤+በእሱም ይኮራል።’” ኤርምያስ 9:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 “ከዚህ ይልቅ የሚኩራራ በዚህ ነገር ይኩራራ፦ ስለ እኔ ጥልቅ ማስተዋልና እውቀት ያለው በመሆኑ+እንዲሁም በምድር ላይ ታማኝ ፍቅር የማሳየው፣ ደግሞም ፍትሕና ጽድቅ የማሰፍነው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ፤+በእነዚህ ነገሮች ደስ እሰኛለሁና”+ ይላል ይሖዋ።
24 “ከዚህ ይልቅ የሚኩራራ በዚህ ነገር ይኩራራ፦ ስለ እኔ ጥልቅ ማስተዋልና እውቀት ያለው በመሆኑ+እንዲሁም በምድር ላይ ታማኝ ፍቅር የማሳየው፣ ደግሞም ፍትሕና ጽድቅ የማሰፍነው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ፤+በእነዚህ ነገሮች ደስ እሰኛለሁና”+ ይላል ይሖዋ።