-
2 ሳሙኤል 7:12-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 14 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ጥፋት በሚያጠፋበት ጊዜም በሰዎች በትር፣ በሰው* ልጆች አለንጋ እቀጣዋለሁ።+ 15 ከፊትህ ካስወገድኩት ከሳኦል ላይ ታማኝ ፍቅሬን እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አይወሰድም። 16 ቤትህና መንግሥትህ ለዘላለም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘላለም የጸና ይሆናል።”’”+
17 ናታንም ይህን ቃል ሁሉና ይህን ራእይ በሙሉ ለዳዊት ነገረው።+
-
-
1 ነገሥት 9:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘር ሐረግህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይታጣም’ በማለት በገባሁለት ቃል መሠረት የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።+
-