ኢሳይያስ 11:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ከእሴይ+ ጉቶ፣ ቅርንጫፍ ይወጣል፤ከሥሮቹም የሚወጣው ቀንበጥ ፍሬ ያፈራል።+ ኢሳይያስ 53:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እሱ በፊቱ* እንደ ቅርንጫፍ፣+ በደረቅ ምድር እንዳለ ሥር ይበቅላል። የሚያምር ቁመናም ሆነ ግርማ ሞገስ የለውም፤+ባየነውም ጊዜ መልኩ አልሳበንም።* ኤርምያስ 33:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ ለዳዊት ቀንበጥ* ይኸውም ጻድቅ ቀንበጥ አበቅላለሁ፤+ እሱም በምድሪቱ ላይ ፍትሕንና ጽድቅን ያሰፍናል።+ 16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ትድናለች፤+ ኢየሩሳሌምም ያለስጋት ትቀመጣለች።+ እሷም “ይሖዋ ጽድቃችን ነው” ተብላ ትጠራለች።’”+ ዘካርያስ 3:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “‘ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ ሆይ፣ አንተም ሆንክ በፊትህ የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ እባካችሁ ስሙ፤ እነዚህ ሰዎች ምልክት ሆነው ያገለግላሉና፤ እነሆ፣ ቀንበጥ+ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ!+ ማቴዎስ 2:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ደግሞም “የናዝሬት ሰው* ይባላል” ተብሎ በነቢያት የተነገረው+ ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት+ ወደምትባል ከተማ መጥቶ መኖር ጀመረ።
15 ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ ለዳዊት ቀንበጥ* ይኸውም ጻድቅ ቀንበጥ አበቅላለሁ፤+ እሱም በምድሪቱ ላይ ፍትሕንና ጽድቅን ያሰፍናል።+ 16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ትድናለች፤+ ኢየሩሳሌምም ያለስጋት ትቀመጣለች።+ እሷም “ይሖዋ ጽድቃችን ነው” ተብላ ትጠራለች።’”+
8 “‘ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ ሆይ፣ አንተም ሆንክ በፊትህ የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ እባካችሁ ስሙ፤ እነዚህ ሰዎች ምልክት ሆነው ያገለግላሉና፤ እነሆ፣ ቀንበጥ+ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ!+