-
ዘፍጥረት 49:8-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 “ይሁዳ+ ሆይ፣ ወንድሞችህ ያወድሱሃል።+ እጅህ የጠላቶችህን አንገት ያንቃል።+ የአባትህ ወንዶች ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።+ 9 ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው።+ ልጄ፣ በእርግጥም ያደንከውን በልተህ ትነሳለህ። እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ እንደ አንበሳ ይንጠራራል፤ ማንስ ሊያስነሳው ይደፍራል? 10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+ 11 አህያውን በወይን ተክል ላይ፣ ውርንጭላውንም ምርጥ በሆነ የወይን ተክል ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጎናጸፊያውንም በወይን ፍሬ ጭማቂ ያጥባል። 12 ዓይኖቹ ከወይን ጠጅ የተነሳ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት የተነሳ የነጡ ናቸው።
-
-
ዕብራውያን 7:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የታወቀ ነውና፤+ ይሁንና ሙሴ ከዚህ ነገድ ካህናት እንደሚገኙ የተናገረው ነገር የለም።
-