-
1 ነገሥት 8:46-50አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
46 “በአንተ ላይ ኃጢአት ቢሠሩ (መቼም ኃጢአት የማይሠራ ሰው የለም)፣+ አንተም በእነሱ እጅግ ተቆጥተህ ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ ጠላቶቻቸውም ራቅ ወዳለ ወይም ቅርብ ወደሆነ የጠላት ምድር ምርኮኛ አድርገው ቢወስዷቸው+ 47 እነሱም በምርኮ በተወሰዱበት ምድር ወደ ልቦናቸው ቢመለሱና+ ወደ አንተ ዞር በማለት+ ‘ኃጢአት ሠርተናል፤ አጥፍተናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’+ በማለት በተማረኩበት ምድር+ ሆነው ሞገስ ለማግኘት ወደ አንተ ልመና ቢያቀርቡ፣ 48 ማርከው በወሰዷቸው ጠላቶቻቸውም ምድር ሆነው በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው* ወደ አንተ ቢመለሱ+ እንዲሁም ለአባቶቻቸው በሰጠሃቸው ምድር፣ አንተ በመረጥካት ከተማና ለስምህ በሠራሁት ቤት አቅጣጫ ወደ አንተ ቢጸልዩ+ 49 ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት ያቀረቡትን ልመና ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ+ ስማ፤ ፍረድላቸውም፤ 50 በአንተ ላይ የፈጸሙትን በደል ሁሉ ይቅር በማለት በአንተ ላይ ኃጢአት የሠራውን ሕዝብህን ይቅር በል። የማረኳቸውም ሰዎች እንዲያዝኑላቸው ታደርጋለህ፤ እነሱም ያዝኑላቸዋል+
-