ዘዳግም 10:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የአማልክት አምላክና+ የጌቶች ጌታ እንዲሁም ታላቅ፣ ኃያል፣ የሚያስፈራ፣ ለማንም የማያዳላና+ ጉቦ የማይቀበል አምላክ ነው። ዘዳግም 16:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ፍርድን አታዛባ፤+ አድልዎ አትፈጽም+ ወይም ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራል፤+ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማል።