የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 31:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ደፋርና ብርቱ ሁኑ።+ ከእናንተ ጋር የሚሄደው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው ወይም በፊታቸው አትሸበሩ።+ እሱ አይጥላችሁም ወይም አይተዋችሁም።”+

  • ዘዳግም 31:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 በፊትህ የሚሄደው ይሖዋ ነው፤ እሱ ምንጊዜም ከአንተ ጋር ይሆናል።+ አይጥልህም ወይም አይተውህም። አትፍራ ወይም አትሸበር።”+

  • ኢያሱ 1:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ይህን ሕዝብ ለአባቶቻቸው ልሰጣቸው ወደማልኩላቸው ምድር+ የምታስገባው አንተ ስለሆንክ ደፋርና ብርቱ ሁን።+

  • ኢያሱ 1:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ደፋርና ብርቱ ሁን ብዬ አዝዤህ አልነበረም? አምላክህ ይሖዋ በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር ስለሆነ አትሸበር፤ አትፍራ።”+

  • 2 ነገሥት 6:16, 17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ኤልሳዕ ግን “አይዞህ፣ አትፍራ!+ ከእነሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ”+ አለው። 17 ከዚያም ኤልሳዕ “ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን ክፈትለት”+ በማለት ጸለየ። ይሖዋም ወዲያውኑ የአገልጋዩን ዓይኖች ከፈተ፤ እሱም አየ፤ እነሆ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች+ በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራማውን አካባቢ ሞልተውት ነበር።+

  • 2 ዜና መዋዕል 20:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 እሱም እንዲህ አለ፦ “የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ እናንተም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና ንጉሥ ኢዮሳፍጥ፣ አዳምጡ! ይሖዋ እንዲህ ይላችኋል፦ ‘ከዚህ ታላቅ ሠራዊት የተነሳ አትፍሩ፤ አትሸበሩ፤ ውጊያው የአምላክ እንጂ የእናንተ አይደለምና።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ