ኢዮብ 36:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በእርግጥ አምላክ ኃያል ነው፤+ ደግሞም ማንንም ገሸሽ አያደርግም፤የማስተዋል ችሎታው* ታላቅ ነው። መዝሙር 147:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ጌታችን ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ኃያል ነው፤+ማስተዋሉም ወሰን የለውም።+ ኢሳይያስ 40:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ማስተዋል ለማግኘት ከማን ጋር ተማከረ?የፍትሕን መንገድ ያስተማረውአሊያም እውቀትን ያካፈለው ማን ነው?ደግሞስ የእውነተኛ ማስተዋልን ጎዳና ያሳየው ማን ነው?+ ኤርምያስ 10:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ምድርን በኃይሉ የሠራው፣ፍሬያማ የሆነችውን መሬት በጥበቡ የመሠረተውና+ሰማያትን በማስተዋሉ የዘረጋው እሱ ነው።+ ሮም 11:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ “የይሖዋን* ሐሳብ ማወቅ የቻለ ማን ነው? አማካሪውስ የሆነ ማን ነው?”+
14 ማስተዋል ለማግኘት ከማን ጋር ተማከረ?የፍትሕን መንገድ ያስተማረውአሊያም እውቀትን ያካፈለው ማን ነው?ደግሞስ የእውነተኛ ማስተዋልን ጎዳና ያሳየው ማን ነው?+