ዘፍጥረት 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ሠራው፤+ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤+ ሰውየውም ሕያው ሰው* ሆነ።+ ኢሳይያስ 42:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ሰማያትን የፈጠረውና የዘረጋው፣+ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች ሁሉ የሠራው፣+በላይዋም ለሚኖሩ ሰዎች እስትንፋስን፣+በእሷም ላይ ለሚመላለሱ መንፈስን የሰጠው+እውነተኛው አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ የሐዋርያት ሥራ 17:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 በተጨማሪም ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው+ እሱ ስለሆነ የሚጎድለው ነገር ያለ ይመስል በሰው እጅ አይገለገልም።+
5 ሰማያትን የፈጠረውና የዘረጋው፣+ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች ሁሉ የሠራው፣+በላይዋም ለሚኖሩ ሰዎች እስትንፋስን፣+በእሷም ላይ ለሚመላለሱ መንፈስን የሰጠው+እውነተኛው አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦