መዝሙር 27:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው። ማንን እፈራለሁ?+ ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+ ማን ያሸብረኛል? መዝሙር 56:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣ቃሉን በማወድሰው በይሖዋ፣11 አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም።+ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+ ሮም 8:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንበል? አምላክ ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?+ ዕብራውያን 13:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ስለዚህ በሙሉ ልብ “ይሖዋ* ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።+