መዝሙር 11:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+ የይሖዋ ዙፋን በሰማያት ነው።+ የገዛ ዓይኖቹ ይመለከታሉ፤ ንቁ የሆኑት* ዓይኖቹ የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።+ ምሳሌ 15:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የይሖዋ ዓይኖች በሁሉም ቦታ ናቸው፤ክፉዎችንም ሆነ ጥሩ ሰዎችን ይመለከታሉ።+ ዕብራውያን 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ደግሞም ከአምላክ እይታ የተሰወረ አንድም ፍጥረት የለም፤+ ይልቁንም ተጠያቂዎች በሆንበት+ በእሱ ዓይኖች ፊት ሁሉም ነገር የተራቆተና ገሃድ የወጣ ነው።