ዘፍጥረት 3:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመሬት ስለተገኘህ+ ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ ላብህን እያንጠፈጠፍክ ምግብ ትበላለህ። አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ።”+ ኢዮብ 34:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እሱ ትኩረቱን* በእነሱ ላይ ቢያደርግ፣መንፈሳቸውንና እስትንፋሳቸውን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፣+15 ሰዎች* ሁሉ በአንድነት በጠፉ፣የሰውም ዘር ወደ አፈር በተመለሰ ነበር።+ መዝሙር 146:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በመኳንንትም* ሆነማዳን በማይችሉ ሰዎች አትታመኑ።+ 4 መንፈሱ* ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤+በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።+ መክብብ 3:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የሰው ልጆች ፍጻሜና* የእንስሳት ፍጻሜ ተመሳሳይ ነውና፤ የሁሉም ፍጻሜ አንድ ነው።+ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው።+ በመሆኑም ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነውና። 20 ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ።+ ሁሉም የተገኙት ከአፈር ነው፤+ ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳሉ።+ መክብብ 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አፈር ቀድሞ ወደነበረበት መሬት ይመለሳል፤+ መንፈስም* ወደ ሰጪው፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ይመለሳል።+
14 እሱ ትኩረቱን* በእነሱ ላይ ቢያደርግ፣መንፈሳቸውንና እስትንፋሳቸውን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፣+15 ሰዎች* ሁሉ በአንድነት በጠፉ፣የሰውም ዘር ወደ አፈር በተመለሰ ነበር።+
19 የሰው ልጆች ፍጻሜና* የእንስሳት ፍጻሜ ተመሳሳይ ነውና፤ የሁሉም ፍጻሜ አንድ ነው።+ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው።+ በመሆኑም ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነውና። 20 ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ።+ ሁሉም የተገኙት ከአፈር ነው፤+ ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳሉ።+