መዝሙር 86:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጥሩ ነህና፤+ ይቅር ለማለትም ዝግጁ ነህ፤+አንተን ለሚጠሩ ሁሉ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ወሰን የለውም።+ ማርቆስ 10:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ለምን ጥሩ ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ጥሩ የለም።+