መዝሙር 86:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጥሩ ነህና፤+ ይቅር ለማለትም ዝግጁ ነህ፤+አንተን ለሚጠሩ ሁሉ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ወሰን የለውም።+ ማቴዎስ 19:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 እሱም “ስለ ጥሩ ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? ጥሩ የሆነው አምላክ ብቻ ነው።+ ሆኖም ሕይወት ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ዘወትር ትእዛዛቱን ጠብቅ” አለው።+ ሉቃስ 18:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ለምን ጥሩ ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ጥሩ የለም።+