መዝሙር 43:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ብርሃንህንና እውነትህን ላክ።+ እነሱ ይምሩኝ፤+ወደተቀደሰው ተራራህና ወደ ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ይውሰዱኝ።+ ምሳሌ 6:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ትእዛዙ መብራት ነውና፤+ሕጉም ብርሃን ነው፤+የተግሣጽ ወቀሳም ወደ ሕይወት ይመራል።+ ኢሳይያስ 51:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ሕዝቤ ሆይ፣ በጥሞና አዳምጡኝ፤አንተም የእኔ ብሔር፣ ጆሮህን ስጠኝ።+ ሕግ ከእኔ ይወጣልና፤+የፍትሕ እርምጃዬም ለሕዝቦች እንደ ብርሃን ጸንቶ እንዲቆም አደርጋለሁ።+ ሮም 15:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በምናሳየው ጽናትና+ ከቅዱሳን መጻሕፍት በምናገኘው መጽናኛ ተስፋ ይኖረን ዘንድ+ ቀደም ብሎ የተጻፈው ነገር ሁሉ ለእኛ ትምህርት እንዲሆን ተጽፏልና።+ 2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው፤+ እንዲሁም ለማስተማር፣+ ለመውቀስ፣ ነገሮችን ለማቅናትና* በጽድቅ ለመገሠጽ ይጠቅማሉ፤+ 17 ይኸውም የአምላክ ሰው ለማንኛውም መልካም ሥራ በሚገባ በመታጠቅ ሙሉ በሙሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። 2 ጴጥሮስ 1:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 በመሆኑም ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ጎህ እስኪቀድና የንጋት ኮከብ+ እስኪወጣ ድረስ በጨለማ ቦታ፣ በልባችሁ ውስጥ ለሚበራ መብራት+ የምትጠነቀቁትን ያህል ለትንቢታዊው ቃል ትኩረት መስጠታችሁ መልካም ነው።
4 ሕዝቤ ሆይ፣ በጥሞና አዳምጡኝ፤አንተም የእኔ ብሔር፣ ጆሮህን ስጠኝ።+ ሕግ ከእኔ ይወጣልና፤+የፍትሕ እርምጃዬም ለሕዝቦች እንደ ብርሃን ጸንቶ እንዲቆም አደርጋለሁ።+
16 ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው፤+ እንዲሁም ለማስተማር፣+ ለመውቀስ፣ ነገሮችን ለማቅናትና* በጽድቅ ለመገሠጽ ይጠቅማሉ፤+ 17 ይኸውም የአምላክ ሰው ለማንኛውም መልካም ሥራ በሚገባ በመታጠቅ ሙሉ በሙሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው።
19 በመሆኑም ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ጎህ እስኪቀድና የንጋት ኮከብ+ እስኪወጣ ድረስ በጨለማ ቦታ፣ በልባችሁ ውስጥ ለሚበራ መብራት+ የምትጠነቀቁትን ያህል ለትንቢታዊው ቃል ትኩረት መስጠታችሁ መልካም ነው።