2 ሳሙኤል 7:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 2 ሳሙኤል 7:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ቤትህና መንግሥትህ ለዘላለም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘላለም የጸና ይሆናል።”’”+ 1 ዜና መዋዕል 17:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “ ‘ “የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ ከአባቶችህ ጋር ለመሆን በምትሄድበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ዘርህን ይኸውም ከወንዶች ልጆችህ መካከል አንዱን አስነሳለሁ፤+ ንግሥናውንም አጸናለሁ።+ 12 ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አጸናለሁ።+ መዝሙር 89:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤+በተቀደሰ ዘይቴም ቀባሁት።+ መዝሙር 89:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ዘሩን ለዘላለም አጸናለሁ፤ዙፋኑም የሰማያትን ዕድሜ ያህል ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።+
11 “ ‘ “የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ ከአባቶችህ ጋር ለመሆን በምትሄድበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ዘርህን ይኸውም ከወንዶች ልጆችህ መካከል አንዱን አስነሳለሁ፤+ ንግሥናውንም አጸናለሁ።+ 12 ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አጸናለሁ።+