ዘፍጥረት 15:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚህ በኋላ የይሖዋ ቃል በራእይ ወደ አብራም መጥቶ “አብራም አትፍራ።+ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ።+ የምታገኘውም ሽልማት እጅግ ታላቅ ይሆናል”+ አለው። 2 ሳሙኤል 22:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤+ጋሻዬ፣+ የመዳኔ ቀንድና* አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤+መሸሻዬና+ አዳኜ ነው፤+ አንተ ከዓመፅ ታድነኛለህ። መዝሙር 3:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን በዙሪያዬ ያለህ ጋሻ ነህ፤+አንተ ክብሬና+ ራሴን ቀና የምታደርግ ነህ።+