6 በይሖዋ ፊት ምን ይዤ ልቅረብ?
ከፍ ባለ ስፍራ በሚኖረው አምላክ ፊት ምን ይዤ ልስገድ?
ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና
የአንድ ዓመት ጥጃዎች ይዤ ልቅረብ?+
7 ይሖዋ በሺህ በሚቆጠሩ አውራ በጎች
ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋል?+
ለሠራሁት በደል የበኩር ወንድ ልጄን፣
ለሠራሁትም ኃጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብ?+
8 ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል።
ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ፍትሕን እንድታደርግ፣+ ታማኝነትን እንድትወድና+
ልክህን አውቀህ+ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው!+