2 ዜና መዋዕል 16:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 አዎ፣ በሙሉ ልባቸው ወደ እሱ ላዘነበሉት ሰዎች*+ ብርታቱን ያሳይ ዘንድ* የይሖዋ ዓይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመላለሳሉ።+ በዚህ ረገድ የሞኝነት ድርጊት ፈጽመሃል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይለይህም።”+ መዝሙር 11:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+ የይሖዋ ዙፋን በሰማያት ነው።+ የገዛ ዓይኖቹ ይመለከታሉ፤ ንቁ የሆኑት* ዓይኖቹ የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።+ መዝሙር 17:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ልቤን መረመርክ፤ በሌሊት በሚገባ አጤንከኝ፤+ደግሞም አጠራኸኝ፤+አንዳች መጥፎ ነገር እንዳላሰብኩ ታውቃለህ፤አንደበቴም አልበደለም። ኤርምያስ 17:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እኔ ይሖዋ፣ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ፣እንደ ሥራውም ፍሬ ለመስጠትልብን እመረምራለሁ፤+የውስጥ ሐሳብንም* እፈትናለሁ።+ ዕብራውያን 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ደግሞም ከአምላክ እይታ የተሰወረ አንድም ፍጥረት የለም፤+ ይልቁንም ተጠያቂዎች በሆንበት+ በእሱ ዓይኖች ፊት ሁሉም ነገር የተራቆተና ገሃድ የወጣ ነው።
9 አዎ፣ በሙሉ ልባቸው ወደ እሱ ላዘነበሉት ሰዎች*+ ብርታቱን ያሳይ ዘንድ* የይሖዋ ዓይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመላለሳሉ።+ በዚህ ረገድ የሞኝነት ድርጊት ፈጽመሃል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይለይህም።”+