13 ማስተዋል የጎደላት ሴት ጯኺ ናት።+
እሷ ጨርሶ ማመዛዘን አትችልም፤ ደግሞም አንዳች ነገር አታውቅም።
14 በከተማዋ ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ፣
በቤቷ ደጃፍ ወንበር ላይ ትቀመጣለች፤+
15 በጎዳናው የሚያልፉትን፣
ቀጥ ብለው በመንገዳቸው የሚሄዱትን ትጣራለች፦
16 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።”
ማስተዋል ለጎደላቸው ሁሉ እንዲህ ትላለች፦+
17 “የተሰረቀ ውኃ ይጣፍጣል፤
ተደብቀው የበሉት ምግብም ይጥማል።”+
18 እሱ ግን በሞት የተረቱት በዚያ እንዳሉ፣
እንግዶቿም በመቃብር ጥልቅ ውስጥ እንደሚገኙ አያውቅም።+