7 አሁንም አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ገና አንድ ፍሬ ልጅና ተሞክሮ የሌለኝ+ ብሆንም አገልጋይህን በአባቴ በዳዊት ምትክ አንግሠኸዋል። 8 አገልጋይህ አንተ በመረጥከው፣+ ከብዛቱም የተነሳ ሊቆጠር በማይችለው ሕዝብ መካከል ይገኛል። 9 ስለሆነም አገልጋይህ ሕዝብህን መዳኘት እንዲሁም መልካምና ክፉ የሆነውን ነገር መለየት+ እንዲችል ታዛዥ ልብ ስጠው፤+ አለዚያማ ስፍር ቁጥር የሌለውን ይህን ሕዝብህን ማን ሊዳኝ ይችላል?”