ዘፀአት 20:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም+ አባትህንና እናትህን አክብር።+ ዘፀአት 21:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ይገደል።+ ማቴዎስ 15:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እናንተ ግን እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን “እናንተን መጦር የምችልበት፣ ያለኝ ነገር ሁሉ ለአምላክ የተወሰነ ስጦታ ነው”+ ካለ 6 አባቱን የማክበር ግዴታ የለበትም።’ በመሆኑም ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ቃል ሽራችኋል።+ ኤፌሶን 6:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ልጆች ሆይ፣ ከጌታ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤+ ይህ የጽድቅ ተግባር ነውና።
5 እናንተ ግን እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን “እናንተን መጦር የምችልበት፣ ያለኝ ነገር ሁሉ ለአምላክ የተወሰነ ስጦታ ነው”+ ካለ 6 አባቱን የማክበር ግዴታ የለበትም።’ በመሆኑም ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ቃል ሽራችኋል።+