ኢሳይያስ 65:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ‘እዚያው ባለህበት ሁን፤ አትጠጋኝ፤እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና’* ይላሉ። እነዚህ ሰዎች በአፍንጫዬ እንዳለ ጭስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድ እሳት ናቸው። ማቴዎስ 6:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 “ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ+ የጽድቅ ሥራችሁን በእነሱ ፊት እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ምንም ብድራት አታገኙም። ሮም 10:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የአምላክን ጽድቅ ሳያውቁ+ የራሳቸውን ጽድቅ ለመመሥረት+ ስለፈለጉ ራሳቸውን ለአምላክ ጽድቅ አላስገዙም።+ ሮም 14:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ታዲያ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ?+ አንተ ደግሞ ወንድምህን ለምን ትንቃለህ? ሁላችንም በአምላክ የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።+