ምሳሌ 21:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ጥበበኛ ሰው የኃያላን ሰዎች ከተማ ላይ ይወጣል፤*የሚታመኑበትንም ብርታት ያዳክማል።+ ምሳሌ 24:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ጥበበኛ ሰው ኃያል ነው፤+ሰውም በእውቀት ኃይሉን ይጨምራል። መክብብ 7:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ገንዘብ ጥበቃ እንደሚያስገኝ+ ሁሉ ጥበብም ጥበቃ ታስገኛለችና፤+ የእውቀት ብልጫ ግን፣ ጥበብ የባለቤቷን ሕይወት ጠብቃ ማቆየት መቻሏ ነው።+ መክብብ 7:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ጥበብ ጥበበኛውን ሰው፣ በአንድ ከተማ ካሉ አሥር ብርቱ ሰዎች ይበልጥ ኃያል ታደርገዋለች።+ መክብብ 9:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከጦር መሣሪያ ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካም ነገርን ሊያጠፋ ይችላል።+