-
2 ሳሙኤል 12:9-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ታዲያ በፊቱ መጥፎ ነገር በመሥራት የይሖዋን ቃል ያቃለልከው ለምንድን ነው? ሂታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታኸው!+ በአሞናውያን ሰይፍ ከገደልከውም+ በኋላ ሚስቱን ወስደህ ሚስትህ አደረግካት።+ 10 ስለዚህ የሂታዊውን የኦርዮን ሚስት ወስደህ ሚስትህ በማድረግ እኔን ስለናቅክ ሰይፍ ከቤትህ ፈጽሞ አይለይም።’+ 11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከገዛ ቤትህ መከራ አመጣብሃለሁ፤+ ዓይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለሌላ ሰው* እሰጣቸዋለሁ፤+ እሱም በቀን ብርሃን* ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።+
-