መዝሙር 39:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በእርግጥም ሰው ሁሉ የሚመላለሰው እንደ ጥላ ነው። ላይ ታች የሚለው* በከንቱ ነው። ማን እንደሚጠቀምበት ሳያውቅ ንብረት ያከማቻል።+ ሉቃስ 12:18-20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከዚያም እንዲህ አለ፦ ‘እንዲህ አደርጋለሁ፦+ ያሉኝን ጎተራዎች አፈርስና ትላልቅ ጎተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም እህሌንና ንብረቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ 19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+
18 ከዚያም እንዲህ አለ፦ ‘እንዲህ አደርጋለሁ፦+ ያሉኝን ጎተራዎች አፈርስና ትላልቅ ጎተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም እህሌንና ንብረቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ 19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+