13 እንግዲህ እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ከተማ እንሄዳለን፤ እዚያም ዓመት እንቆያለን፤ እንነግዳለን እንዲሁም እናተርፋለን” የምትሉ ስሙ፤+ 14 ሕይወታችሁ ነገ ምን እንደሚሆን እንኳ አታውቁም።+ ለጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁና።+ 15 ከዚህ ይልቅ “ይሖዋ ከፈቀደ+ በሕይወት እንኖራለን፤ ደግሞም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል። 16 አሁን ግን እናንተ ከልክ በላይ ጉራ በመንዛት ትኩራራላችሁ። እንዲህ ያለው ጉራ ሁሉ ክፉ ነው።