6 ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር የሚቀመጥበት ጊዜ ይኖራል፤+
ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤
ጥጃ፣ አንበሳና የሰባ ከብት አብረው ይሆናሉ፤+
ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
7 ላምና ድብ አብረው ይበላሉ፤
ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ።
አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል።+
8 ጡት የሚጠባ ሕፃንም በእባብ ጉድጓድ ላይ ይጫወታል፤
ጡት የጣለውም ሕፃን እጁን በመርዘኛ እባብ ጎሬ ላይ ያደርጋል።
9 በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ
ምንም ዓይነት ጉዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤+
ምክንያቱም ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን
ምድርም በይሖዋ እውቀት ትሞላለች።+