ዘፍጥረት 49:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+ መዝሙር 2:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እንዲህም ይላቸዋል፦ “እኔ ራሴ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን+ ላይንጉሤን ሾምኩ።”+ ዘካርያስ 6:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚገነባው እሱ ነው፤ ግርማ የሚጎናጸፈውም እሱ ነው። በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ ደግሞም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ካህን ሆኖ ያገለግላል፤+ በሁለቱም መካከል* ሰላማዊ ስምምነት ይኖራል። ሉቃስ 22:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 አባቴ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን እንዳደረገ ሁሉ እኔም ከእናንተ ጋር ለመንግሥት ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ ራእይ 19:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 በመደረቢያው አዎ፣ በጭኑ ላይ “የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ”+ የሚል ስም ተጽፏል።
13 የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚገነባው እሱ ነው፤ ግርማ የሚጎናጸፈውም እሱ ነው። በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ ደግሞም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ካህን ሆኖ ያገለግላል፤+ በሁለቱም መካከል* ሰላማዊ ስምምነት ይኖራል።