የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 132:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤

      የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦

      “ከዘሮችህ መካከል አንዱን*

      በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+

  • ኢሳይያስ 53:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  2 እሱ በፊቱ* እንደ ቅርንጫፍ፣+ በደረቅ ምድር እንዳለ ሥር ይበቅላል።

      የሚያምር ቁመናም ሆነ ግርማ ሞገስ የለውም፤+

      ባየነውም ጊዜ መልኩ አልሳበንም።*

  • ኤርምያስ 23:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 “እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ* የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤+ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።+

  • ኤርምያስ 33:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ ለዳዊት ቀንበጥ* ይኸውም ጻድቅ ቀንበጥ አበቅላለሁ፤+ እሱም በምድሪቱ ላይ ፍትሕንና ጽድቅን ያሰፍናል።+

  • ዘካርያስ 3:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 “‘ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ ሆይ፣ አንተም ሆንክ በፊትህ የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ እባካችሁ ስሙ፤ እነዚህ ሰዎች ምልክት ሆነው ያገለግላሉና፤ እነሆ፣ ቀንበጥ+ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ!+

  • ዘካርያስ 6:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 እንዲህም በለው፦

      “‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ቀንበጥ ተብሎ የሚጠራው ሰው ይህ ነው።+ እሱ በገዛ ቦታው ላይ ያቆጠቁጣል፤ የይሖዋንም ቤተ መቅደስ ይሠራል።+

  • ራእይ 5:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ሆኖም ከሽማግሌዎቹ አንዱ “አታልቅስ። እነሆ፣ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፣+ የዳዊት+ ሥር+ ድል ስላደረገ+ ሰባቱን ማኅተሞችና ጥቅልሉን ሊከፍት ይችላል” አለኝ።

  • ራእይ 22:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 “‘እኔ ኢየሱስ ለጉባኤዎቹ ጥቅም ስል ስለ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ለመመሥከር መልአኬን ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር+ እንዲሁም ደማቅ አጥቢያ ኮከብ+ ነኝ።’”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ