የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 8:25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 አሁንም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ ‘አንተ በፊቴ እንደተመላለስከው ሁሉ ልጆችህም በጥንቃቄ በፊቴ ከተመላለሱ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከፊቴ ፈጽሞ አይታጣም’ በማለት ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቅ።+

  • መዝሙር 89:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 አንተም እንዲህ ብለሃል፦ “ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፤+

      ለአገልጋዬ ለዳዊት ምያለሁ፦+

       4 ‘ዘርህ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ፤+

      ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’”+ (ሴላ)

  • መዝሙር 89:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤+

      በተቀደሰ ዘይቴም ቀባሁት።+

  • መዝሙር 89:36
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 36 ዘሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤+

      ዙፋኑ በፊቴ እንዳለችው ፀሐይ ይጸናል።+

  • ኢሳይያስ 9:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 በዳዊት ዙፋንና+ በመንግሥቱ ላይ ይቀመጣል፤

      እየተጠናከረ የሚሄደው አገዛዙም* ሆነ

      ሰላሙ ፍጻሜ አይኖረውም።+

      ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም

      በማይናወጥ ሁኔታ ይመሠረታል፤+

      በፍትሕና+ በጽድቅም+ ጸንቶ ይኖራል።

      የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

  • ኤርምያስ 33:20, 21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ፣ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ የምትችሉ ከሆነ፣+ 21 ያን ጊዜ ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋር የገባሁት ቃል ኪዳኔ ሊፈርስ ይችላል፤+ ያን ጊዜ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ አይኖረውም፤+ አገልጋዮቼ ከሆኑት ከሌዋውያን ካህናት+ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ይፈርሳል።

  • ማቴዎስ 9:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ ሁለት ዓይነ ስውሮች+ “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልን” ብለው እየጮኹ ተከተሉት።

  • ሉቃስ 1:69
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 69 ደግሞም በአገልጋዩ በዳዊት ቤት+ የመዳን ቀንድ* አስነስቶልናል፤+

  • የሐዋርያት ሥራ 2:30, 31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 እሱ ነቢይ ስለነበረና አምላክ ከዘሮቹ አንዱን* በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል እንደገባለት ስላወቀ+ 31 አምላክ ክርስቶስን በመቃብር* እንደማይተወውና ሥጋውም እንደማይበሰብስ* አስቀድሞ ተረድቶ ስለ ትንሣኤው ተናገረ።+

  • የሐዋርያት ሥራ 13:22, 23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 እሱን ከሻረው በኋላ ‘እንደ ልቤ የሆነውን+ የእሴይን+ ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤ እሱ የምፈልገውን ነገር ሁሉ ያደርጋል’ ሲል የመሠከረለትን ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ አስነሳላቸው።+ 23 አምላክ በገባው ቃል መሠረት ከዚህ ሰው ዘር ለእስራኤል አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን አመጣ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ