2 ዜና መዋዕል 36:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ስለዚህ የከለዳውያንን+ ንጉሥ አመጣባቸው፤ እሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሳቸው+ ውስጥ በሰይፍ ገደለ፤+ ለወጣቱም ሆነ ለድንግሊቱ፣ ለሽማግሌውም ሆነ ለአቅመ ደካማው አልራራም።+ አምላክ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።+ ኤርምያስ 51:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ባቢሎን በይሖዋ እጅ ያለች የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ምድርን ሁሉ አሰከረች። ብሔራት ወይን ጠጇን ጠጥተው ሰከሩ፤+ብሔራት ያበዱት ለዚህ ነው።+ ሕዝቅኤል 29:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ የግብፅን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣለሁ፤+ እሱም ሀብቷን ያግዛል፤ በእጅጉ ይበዘብዛል እንዲሁም ይመዘብራል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደሞዝ ይሆናል።’ ዳንኤል 5:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ንጉሥ ሆይ፣ ልዑሉ አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነጾር መንግሥት፣ ታላቅነት፣ ክብርና ግርማ ሰጠው።+ 19 ታላቅነትን ስላጎናጸፈው ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጡ ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር።+ የፈለገውን ይገድል ወይም በሕይወት እንዲኖር ይፈቅድ፣ የፈለገውን ከፍ ከፍ ያደርግ ወይም ያዋርድ ነበር።+
17 ስለዚህ የከለዳውያንን+ ንጉሥ አመጣባቸው፤ እሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሳቸው+ ውስጥ በሰይፍ ገደለ፤+ ለወጣቱም ሆነ ለድንግሊቱ፣ ለሽማግሌውም ሆነ ለአቅመ ደካማው አልራራም።+ አምላክ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።+
19 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ የግብፅን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣለሁ፤+ እሱም ሀብቷን ያግዛል፤ በእጅጉ ይበዘብዛል እንዲሁም ይመዘብራል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደሞዝ ይሆናል።’
18 ንጉሥ ሆይ፣ ልዑሉ አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነጾር መንግሥት፣ ታላቅነት፣ ክብርና ግርማ ሰጠው።+ 19 ታላቅነትን ስላጎናጸፈው ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጡ ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር።+ የፈለገውን ይገድል ወይም በሕይወት እንዲኖር ይፈቅድ፣ የፈለገውን ከፍ ከፍ ያደርግ ወይም ያዋርድ ነበር።+