ኤርምያስ 25:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* እጠራለሁ፤+ በዚህች ምድር፣ በነዋሪዎቿና በዙሪያዋ ባሉ በእነዚህ ብሔራት ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ።+ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤ እንዲሁም መቀጣጫና ማፏጫ እንዲሆኑ ብሎም ባድማ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋለሁ። ዳንኤል 3:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 አዋጅ ነጋሪው ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጣችሁ ሕዝቦች ሆይ፣ እንዲህ እንድታደርጉ ታዛችኋል፦ 5 የቀንደ መለከት፣ የእምቢልታ፣ የተለያዩ ባለ አውታር መሣሪያዎች፣ የባለ ሦስት ማዕዘን በገና፣ የባለ ከረጢት ዋሽንትና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ በግንባራችሁ ተደፍታችሁ ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመው የወርቅ ምስል ስገዱ። ዳንኤል 4:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ንጉሥ ሆይ፣ አንተ ነህ፤ ምክንያቱም አንተ ታላቅና ብርቱ ሆነሃል፤ ታላቅነትህ ገንኖ እስከ ሰማያት ደርሷል፤+ ግዛትህም እስከ ምድር ዳርቻ ተንሰራፍቷል።+
9 የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* እጠራለሁ፤+ በዚህች ምድር፣ በነዋሪዎቿና በዙሪያዋ ባሉ በእነዚህ ብሔራት ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ።+ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤ እንዲሁም መቀጣጫና ማፏጫ እንዲሆኑ ብሎም ባድማ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋለሁ።
4 አዋጅ ነጋሪው ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጣችሁ ሕዝቦች ሆይ፣ እንዲህ እንድታደርጉ ታዛችኋል፦ 5 የቀንደ መለከት፣ የእምቢልታ፣ የተለያዩ ባለ አውታር መሣሪያዎች፣ የባለ ሦስት ማዕዘን በገና፣ የባለ ከረጢት ዋሽንትና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ በግንባራችሁ ተደፍታችሁ ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመው የወርቅ ምስል ስገዱ።