ኤርምያስ 51:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “ፍላጻዎቻችሁን አሹሉ፤+ ክብ የሆኑትን ጋሻዎች አንሱ።* ይሖዋ የሜዶናውያንን ነገሥታት መንፈስ አነሳስቷል፤+ምክንያቱም ባቢሎንን ለማጥፋት አስቧል። ይህ የይሖዋ በቀል ይኸውም ስለ ቤተ መቅደሱ የሚወስደው የበቀል እርምጃ ነውና። ኤርምያስ 51:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ብሔራትን፣ የሜዶንን+ ነገሥታት፣ ገዢዎቿን፣ የበታች ገዢዎቿን ሁሉናበእያንዳንዳቸው ግዛት ሥር ያለውን ምድር ሁሉበእሷ ላይ እንዲዘምቱ መድቧቸው።* ዳንኤል 5:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 “ፊሬስ ማለት ደግሞ መንግሥትህ ተከፈለ፤ ለሜዶናውያንና ለፋርሳውያን ተሰጠ ማለት ነው።”+ ዳንኤል 5:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 በዚያኑ ሌሊት ከለዳዊው ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ።+
11 “ፍላጻዎቻችሁን አሹሉ፤+ ክብ የሆኑትን ጋሻዎች አንሱ።* ይሖዋ የሜዶናውያንን ነገሥታት መንፈስ አነሳስቷል፤+ምክንያቱም ባቢሎንን ለማጥፋት አስቧል። ይህ የይሖዋ በቀል ይኸውም ስለ ቤተ መቅደሱ የሚወስደው የበቀል እርምጃ ነውና።