የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 25:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ስለዚህ ከይሖዋ እጅ ጽዋውን ወሰድኩ፤ ይሖዋ ወደላከኝም ብሔራት ሁሉ ሄጄ አጠጣኋቸው፦+

  • ኤርምያስ 25:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 የጢሮስ ነገሥታት ሁሉ፣ የሲዶና+ ነገሥታት ሁሉና በባሕሩ ላይ ያለው ደሴት ነገሥታት፣

  • ኤርምያስ 47:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ምክንያቱም የሚመጣው ቀን ፍልስጤማውያንን+ ሁሉ ያጠፋል፤

      በሕይወት ተርፈው ጢሮስንና+ ሲዶናን+ የሚረዱትን ሁሉ ያስወግዳል።

      ይሖዋ ፍልስጤማውያንን

      ይኸውም ከካፍቶር*+ ደሴት የመጡ ቀሪዎችን ያጠፋልና።

  • ሕዝቅኤል 26:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ፣ እነሆ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ባሕር ሞገዱን እንደሚያስነሳ ብዙ ብሔራትን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ።

  • ሕዝቅኤል 27:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጢሮስ ላይ ሙሾ አውርድ፤*+

  • ኢዩኤል 3:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ጢሮስ፣ ሲዶና እና የፍልስጤም ግዛቶች ሁሉ፣

      ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አላችሁ?

      ላደረግኩባችሁ ነገር ብድራት ልትመልሱልኝ ነው?

      ብድራት የምትመልሱልኝ ከሆነ

      ብድራታችሁን ወዲያውኑ፣ በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።+

  • አሞጽ 1:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  9 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      ‘ስለ ሦስቱ የጢሮስ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤

      ምክንያቱም ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤

      ደግሞም የወንድማማቾችን ቃል ኪዳን አላስታወሱም።+

      10 በመሆኑም በጢሮስ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤

      የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል።’+

  • ዘካርያስ 9:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 ጢሮስ የመከላከያ ግንብ* ገንብታለች።

      ብርን እንደ አቧራ፣

      ወርቅንም በመንገድ ላይ እንዳለ አፈር ቆልላለች።+

      4 እነሆ፣ ይሖዋ ንብረቷን ይወስዳል፤

      ሠራዊቷንም ባሕሩ ውስጥ* ይደመስሳል፤+

      እሷም በእሳት ትበላለች።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ