የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 23:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 እሱም እንዲህ ይላል፦ “አንቺ የተጨቆንሽ የሲዶና ድንግል ሆይ፣

      ዳግመኛ ሐሴት አታደርጊም።+

      ተነሽ፣ ወደ ኪቲም+ ተሻገሪ።

      እዚያም ቢሆን እረፍት አታገኚም።”

  • ኤርምያስ 47:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ምክንያቱም የሚመጣው ቀን ፍልስጤማውያንን+ ሁሉ ያጠፋል፤

      በሕይወት ተርፈው ጢሮስንና+ ሲዶናን+ የሚረዱትን ሁሉ ያስወግዳል።

      ይሖዋ ፍልስጤማውያንን

      ይኸውም ከካፍቶር*+ ደሴት የመጡ ቀሪዎችን ያጠፋልና።

  • ሕዝቅኤል 25:15-17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ፍልስጤማውያን በማይበርድ የጠላትነት ስሜት ተነሳስተው በክፋት* የበቀል እርምጃ ለመውሰድና ጥፋት ለማድረስ ጥረት አድርገዋል።+ 16 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በፍልስጤማውያን ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤+ ከሪታውያንንም አጠፋለሁ፤+ በባሕሩ ዳርቻ ላይ የቀሩትንም ነዋሪዎች እደመስሳለሁ።+ 17 ኃይለኛ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ የበቀል እርምጃ እወስድባቸዋለሁ፤ በምበቀላቸውም ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”

  • አሞጽ 1:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  9 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      ‘ስለ ሦስቱ የጢሮስ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤

      ምክንያቱም ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤

      ደግሞም የወንድማማቾችን ቃል ኪዳን አላስታወሱም።+

      10 በመሆኑም በጢሮስ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤

      የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል።’+

  • ዘካርያስ 9:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 የፍርድ መልእክት፦

      “የይሖዋ ቃል በሃድራክ ምድር ላይ ነው፤

      ደማስቆንም ዒላማው* አድርጓል፤+

      የይሖዋ ዓይን በሰው ዘርና

      በእስራኤል ነገዶች ሁሉ ላይ ነውና፤+

       2 አዋሳኟ የሆነችውን ሃማትንም+ ዒላማው አድርጓል፤

      ደግሞም እጅግ ጥበበኛ ቢሆኑም+ እንኳ ጢሮስንና+ ሲዶናን+ ዒላማው አድርጓል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ