ኢሳይያስ 29:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በዚያ ቀን፣ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የመጽሐፉን ቃል ይሰማሉ፤የዓይነ ስውራኑም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።+ ኤርምያስ 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው ስለተዘጉ* ማዳመጥ አይችሉም።+ እነሆ፣ የይሖዋን ቃል መሳለቂያ አድርገውታል፤+ቃሉም ደስ አያሰኛቸውም። ማርቆስ 7:32-35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 በዚያም* ሰዎች መስማት የተሳነውና የመናገር እክል ያለበት+ አንድ ሰው ወደ እሱ አምጥተው እጁን እንዲጭንበት ተማጸኑት። 33 እሱም ከሕዝቡ ለይቶ ለብቻው ወሰደው። ከዚያም ጣቶቹን በሰውየው ጆሮዎች ውስጥ አስገባ፤ እንትፍ ካለ በኋላም የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ።+ 34 ወደ ሰማይ እየተመለከተም በረጅሙ ተንፍሶ “ኤፈታ” አለው፤ ይህም “ተከፈት” ማለት ነው። 35 በዚህ ጊዜ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤+ ምላሱም ተፈቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ። ሉቃስ 7:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፦ ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤+ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+
10 “ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው ስለተዘጉ* ማዳመጥ አይችሉም።+ እነሆ፣ የይሖዋን ቃል መሳለቂያ አድርገውታል፤+ቃሉም ደስ አያሰኛቸውም።
32 በዚያም* ሰዎች መስማት የተሳነውና የመናገር እክል ያለበት+ አንድ ሰው ወደ እሱ አምጥተው እጁን እንዲጭንበት ተማጸኑት። 33 እሱም ከሕዝቡ ለይቶ ለብቻው ወሰደው። ከዚያም ጣቶቹን በሰውየው ጆሮዎች ውስጥ አስገባ፤ እንትፍ ካለ በኋላም የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ።+ 34 ወደ ሰማይ እየተመለከተም በረጅሙ ተንፍሶ “ኤፈታ” አለው፤ ይህም “ተከፈት” ማለት ነው። 35 በዚህ ጊዜ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤+ ምላሱም ተፈቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ።
22 እሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፦ ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤+ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+