2 ነገሥት 3:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 እነሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሲመጡ እስራኤላውያን ተነስተው ሞዓባውያንን መምታት ጀመሩ፤ እነሱም ከፊታቸው ሸሹ።+ እስራኤላውያንም ሞዓባውያንን እየመቱ ወደ ሞዓብ ገሰገሱ። 25 ከተሞቹንም ደመሰሱ፤ እያንዳንዱም ሰው ድንጋይ እየጣለ ጥሩውን መሬት ሁሉ በድንጋይ ሞላው፤ የውኃ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤+ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቆረጡ።+ በመጨረሻም የቂርሃረሰት+ የድንጋይ ግንቦች ብቻ ቆመው ቀሩ፤ ወንጭፍ የሚወነጭፉትም ዙሪያዋን ከበው መቷት። ኢሳይያስ 16:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በመሆኑም ሞዓብ፣ ስለ ሞዓብ ዋይ ዋይ ይላል፤አዎ፣ ሁሉም ዋይ ዋይ ይላሉ።+ የተመቱት ሰዎች ስለ ቂርሃረሰት+ የዘቢብ ቂጣ ያለቅሳሉ።
24 እነሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሲመጡ እስራኤላውያን ተነስተው ሞዓባውያንን መምታት ጀመሩ፤ እነሱም ከፊታቸው ሸሹ።+ እስራኤላውያንም ሞዓባውያንን እየመቱ ወደ ሞዓብ ገሰገሱ። 25 ከተሞቹንም ደመሰሱ፤ እያንዳንዱም ሰው ድንጋይ እየጣለ ጥሩውን መሬት ሁሉ በድንጋይ ሞላው፤ የውኃ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤+ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቆረጡ።+ በመጨረሻም የቂርሃረሰት+ የድንጋይ ግንቦች ብቻ ቆመው ቀሩ፤ ወንጭፍ የሚወነጭፉትም ዙሪያዋን ከበው መቷት።