ኢሳይያስ 11:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እስራኤል ከግብፅ ምድር በወጣበት ጊዜ እንደሆነው ሁሉ፣ከሕዝቡ የተረፉት ቀሪዎችም+ ከአሦር የሚወጡበት ጎዳና+ ይኖራል። ኢሳይያስ 65:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እኔን ለሚፈልገኝ ሕዝቤ፣ሳሮን+ የበጎች መሰማሪያ፣የአኮርም ሸለቆ*+ የከብቶች ማረፊያ ይሆናል። ኤርምያስ 23:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 “ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤+ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።+ ኤርምያስ 33:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከይሁዳ የተማረኩትንና ከእስራኤል የተማረኩትን እመልሳለሁ፤+ እንደቀድሞውም እገነባቸዋለሁ።+ ሕዝቅኤል 34:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል።+ በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤+ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።” ሚክያስ 2:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ያዕቆብ ሆይ፣ ሁላችሁንም በእርግጥ እሰበስባለሁ፤ከእስራኤል የቀሩትን ያላንዳች ጥርጥር አንድ ላይ እሰበስባለሁ።+ በጉረኖ ውስጥ እንዳለ በግ፣በግጦሽ መስክ ላይ እንዳለም መንጋ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤+ቦታውም በሕዝብ ሁካታ ይሞላል።’+
3 “ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤+ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።+
14 ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል።+ በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤+ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።”
12 ያዕቆብ ሆይ፣ ሁላችሁንም በእርግጥ እሰበስባለሁ፤ከእስራኤል የቀሩትን ያላንዳች ጥርጥር አንድ ላይ እሰበስባለሁ።+ በጉረኖ ውስጥ እንዳለ በግ፣በግጦሽ መስክ ላይ እንዳለም መንጋ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤+ቦታውም በሕዝብ ሁካታ ይሞላል።’+