7 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
“በታላቅ ደስታ ወደ ያዕቆብ ጩኹ።
ከብሔራት በላይ ስለሆናችሁ እልል በሉ።+
ይህን አውጁ፤ ውዳሴ አቅርቡ፤
ደግሞም ‘ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን፣ የእስራኤልን ቀሪዎች አድን’ በሉ።+
8 ከሰሜን ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ።+
ከምድር ዳርቻዎች እሰበስባቸዋለሁ።+
በመካከላቸው ዓይነ ስውርና አንካሳ፣+
ነፍሰ ጡርና ልትወልድ የተቃረበች ሴት በአንድነት ይገኛሉ።
ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።+