ኢዮብ 12:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 የዘራፊዎች ድንኳን ሰላም አለው፤+አምላክን የሚያስቆጡ ሰዎችም፣አምላካቸውን* በእጃቸው እንደያዙ ሰዎች የደህንነት ስሜት ይሰማቸዋል።+ ኢዮብ 21:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ክፉዎች በሕይወት የሚኖሩት፣+ለእርጅና የሚበቁትና ባለጸጋ* የሚሆኑት ለምንድን ነው?+ መዝሙር 73:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ክፉ ሰዎች ያላቸውን ሰላም በተመለከትኩ ጊዜ፣እብሪተኛ በሆኑ ሰዎች* ቀንቼ ነበርና።+ ኤርምያስ 5:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ወፍረዋል፤ ቆዳቸውም ለስልሷል፤በክፋት ተሞልተዋል። ለራሳቸው ስኬት ሲያስቡአባት ለሌለው ልጅ አይሟገቱም፤+ድሆችንም ፍትሕ ይነፍጋሉ።’”+