ኢሳይያስ 43:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።+ ዘርህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።+ ሕዝቅኤል 34:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።+ ሶፎንያስ 3:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 በዚያን ጊዜ መልሼ አመጣችኋለሁ፤አዎ፣ በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ። ተማርከው የተወሰዱባችሁን ሰዎች በፊታችሁ መልሼ በምሰበስብበት ጊዜ+በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ዝና* እንድታተርፉና እንድትወደሱ አደርጋለሁና”+ ይላል ይሖዋ።
13 ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።+
20 በዚያን ጊዜ መልሼ አመጣችኋለሁ፤አዎ፣ በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ። ተማርከው የተወሰዱባችሁን ሰዎች በፊታችሁ መልሼ በምሰበስብበት ጊዜ+በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ዝና* እንድታተርፉና እንድትወደሱ አደርጋለሁና”+ ይላል ይሖዋ።