ዘሌዋውያን 26:44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 44 ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን በጠላቶቻቸው ምድር በሚቆዩበት ጊዜ ሁሉ እርግፍ አድርጌ አልተዋቸውም፤+ ፈጽሜ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጥላቸውም፤ እንዲህ ባደርግ ከእነሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ማፍረስ ይሆንብኛል፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካቸው ይሖዋ ነኝ። ነህምያ 9:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ከታላቅ ምሕረትህ የተነሳ ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም+ ወይም አልተውካቸውም፤ ምክንያቱም አንተ ሩኅሩኅና* መሐሪ አምላክ ነህ።+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ከይሖዋ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ሙሉ በሙሉ አልጠፋንም፤+ምሕረቱ ፈጽሞ አያልቅምና።+ አሞጽ 9:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ‘እነሆ፣ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ ዓይኖች በኃጢአተኛው መንግሥት ላይ ናቸው፤እሱም ከምድር ገጽ ያጠፋዋል።+ ይሁንና የያዕቆብን ቤት ሙሉ በሙሉ አልደመስስም’+ ይላል ይሖዋ።
44 ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን በጠላቶቻቸው ምድር በሚቆዩበት ጊዜ ሁሉ እርግፍ አድርጌ አልተዋቸውም፤+ ፈጽሜ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጥላቸውም፤ እንዲህ ባደርግ ከእነሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ማፍረስ ይሆንብኛል፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካቸው ይሖዋ ነኝ።
8 ‘እነሆ፣ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ ዓይኖች በኃጢአተኛው መንግሥት ላይ ናቸው፤እሱም ከምድር ገጽ ያጠፋዋል።+ ይሁንና የያዕቆብን ቤት ሙሉ በሙሉ አልደመስስም’+ ይላል ይሖዋ።