11 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ ደግሞም እንከባከባቸዋለሁ።+ 12 የተበታተኑትን በጎቹን አግኝቶ እንደሚመግብ እረኛ በጎቼን እንከባከባለሁ።+ በደመናትና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።+ 13 ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።+