12 “አሁንም ቢሆን” ይላል ይሖዋ፣
“በጾም፣+ በለቅሶና በዋይታ በሙሉ ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ።+
13 ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤+
ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋም ተመለሱ፤
እሱ ሩኅሩኅና መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየና+ ታማኝ ፍቅሩ የበዛ ነውና፤+
ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት መለስ ብሎ ያጤናል።
14 ደግሞም ተመልሶ ጉዳዩን እንደገና በማጤን፣+
ለአምላካችሁ ለይሖዋ የእህል መባና የመጠጥ መባ ማቅረብ ትችሉ ዘንድ
በረከት ያስቀርላችሁ እንደሆነ ማን ያውቃል?