ኢሳይያስ 34:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ሰይፌ በሰማያት በደም ትርሳለችና።+ በኤዶም ይኸውም እንዲጠፋፍርድ ባስተላለፍኩበት ሕዝብ ላይ ትወርዳለች።+ ሕዝቅኤል 25:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ ሕዝቅኤል 35:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነበት ጊዜ ስለተደሰትክ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ።+ የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ አንተም ሆንክ መላው የኤዶም ምድር ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናላችሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” አሞጽ 1:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የኤዶም ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም የገዛ ወንድሙን በሰይፍ አሳዷል፤+ምሕረት ለማሳየትም እንቢተኛ ሆኗል፤በቁጣው ያላንዳች ፋታ ይዘነጣጥላቸዋል፤አሁንም ቢሆን በእነሱ ላይ ቁጣው አልበረደም።+ አብድዩ 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በጥፋታቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር መምጣት አልነበረብህም፤+በጥፋቱ ቀን በደረሰበት መከራ መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤ደግሞም ጥፋት በደረሰበት ቀን ሀብቱን መውሰድ አልነበረብህም።+
13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+
15 የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነበት ጊዜ ስለተደሰትክ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ።+ የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ አንተም ሆንክ መላው የኤዶም ምድር ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናላችሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የኤዶም ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም የገዛ ወንድሙን በሰይፍ አሳዷል፤+ምሕረት ለማሳየትም እንቢተኛ ሆኗል፤በቁጣው ያላንዳች ፋታ ይዘነጣጥላቸዋል፤አሁንም ቢሆን በእነሱ ላይ ቁጣው አልበረደም።+
13 በጥፋታቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር መምጣት አልነበረብህም፤+በጥፋቱ ቀን በደረሰበት መከራ መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤ደግሞም ጥፋት በደረሰበት ቀን ሀብቱን መውሰድ አልነበረብህም።+